ይከሰታል


      

መኖር ካሉትማ  ጊዜን መቁጠሩን

እያዩዩ አለማየት መሽቶ መንጋቱን

ሰምቶ መደንቆሩን የእልፍ አእላፉን

ስቆቃ ሮሮውን በደል ልቅሶውን 

ከዕውነቱ አምባ አለመቆጠር አለመታየቱን

አምኖ አለማመንን በደሉ ግፉን 

ውሸትን ደፍሮ እውነትን ፈርቶ

ጥቅምን አፍቅሮ ህሊናን ከድቶ

በዘመናችን ብዙ ሰው ኒሯል

ድምጹን አጥፍቶ።

ከሰዎች መሀል ሰው ይከሰታል

ለእውነት ኖሮ ሳይፈራ ያልፋል

በታሪክ ዳራ በሰው ልቦና 

የሚሰራለት የማይፈርስ ሀውልት 

የማይረሳ ጣዕመዜማ የሚዘመርለት።

የቅሬታ አልባ  ጸጸት ላልነካት

በክህደት አምባ ጽዋ ላላነሳች  

በንጹሀን ደም  ላልትነካካች

በውሸት ካባ ላልተኮፈስች

እ ውነቱን አቅፋ በዱር ላደረች

በፍቅረንዋይ ላልነሆለለች

በቅጽበተ ፍሰሃ ላልተማለለች

በታሪክ ዳራ በሰው ህሊና የሚስራላት 

የማይፈርስ ሃውልት 

ጊዜማይሽረው ጣእመዜማ ሚዘርላት 

የይቅርታ ወ ፀጸት አልባ ሕይወት‹

የጭለማ ቀን ብርቱ ብርሀን 

ቀኝ  እጁን ዘርጊ በመክራ ቀን

በሞት መካከል አድራሽ መድህኒት 

በደካሞች መካከል ደራሽ በቅጽበት  

በሙታን መህል አስከሬን ቀባሪ 

በትርምስ ውስጥ ስራትን ሠሪ

በእብሪተኞች ውስጥ ጉልበት  ሰባሪ

ከሰዎች መሀል የህሊና ሰው 

 ቦታ ፤ጊዜ ወኩነት የምትከስተው

 ይከሰታል ሰው።

This entry was posted in posts. Bookmark the permalink.