ግለስበዕና


 ግለስብዕና

የሰው ልጅ የማንነት ጉዞ በግል ስብዕና ጀምሮ በግል ስብዕና የሚደመደም ውስብስብ ጉዞ ነው፡፡ሰው ብቻ ሳይሆን ተሆንቶ (nature)በጥቅሉ ከረቂቅ አንድነት (singularity)ወደ ሰፊ ብዝሀነት ብሎም በብዝሀነት ላይ ወደተጻመረ ውስብስብ አንድነት ያደገነና ሁሌም ያለማቋረጥ የሚያድግ ክሰተት ነው፡፡ ይህ በግዙፉ ተጠቅልሎ የተገለጠው ዕውነት በተናጠል የአንድ መሆን ማንነት ባላቸው ቁሳካላትና ሕይወት ማንነትም ጭምር በተዋረድ የሚንጸባረቅ ዕውነት ነው፡፡ በዚህም ከአናሳ ጽንፈአለም(-infinity)እስክ ግዙፉ ጽንፈዓለም (+infinity)በሚከሰቱ ተክለማንነቶች አንድ ራሱን ችሎ የሚቆም ህልውና(entity) ከመሰሎቹ ሲነጻጸር 99 በመቶ ተመሳሳይነት ቢኖረውም 1በመቶ ወይም ያነሰ እርሱን እርሱ የሚያሰኙት ከማንም ሌላ ተሆንቶአዊ አካል ወይንም ህይወት አጉልተው የሚያወጡት ገጽታዎች ነበሩት፤አሉት ይኖሩታልም፡፡ይህ ለምን ሆነ ቢባል ሁሉን ያደረገችው፤ ሁሉም የሚደረግባትና ሁሌም የምታደርግና የሚደረግባት የተሆንቶ ገጾች እንደ መስታወት የተወለወለችና የጸዳ ፊት የሌላትና እንዲያውም አባጣና ጎባጣ፤ ቁልቁለትና አቀበት፤ ረባድና ኮረብታ፤ አዘቅትና ተራራ፤ በረሀና በረዷማ፤ረግረጋማና ጭንጫ፤ ረጣባማና ደረቅ ሌላ ሌላም ሙሉ በሙሉ መቆጠርና ከግንዛቤ የላቁ ተጻረርቶዎች የተሞላች በመሆንዋና እነዚህም ተጻረርቶዎች በምትሆንበትና በምታደርጋቸው ክንዋኔዎች ሁሉ ቦታን፤ ጊዜና ሁኔታን ያካተተ አሻራቸውንና ጠባሳቸውን ስለሚያሳርፉበት እንደየገጠምሽኙ ዝንጉርጉርና እያንዳንዱም የራሱ ልዩ ገጽታና ይዘት እንዲኖረው ሆኖአል ይሆናልም፡፡ የናት ሆድ ዥንጉርጉር የተባለብትም በርግጥም የቀለማት ብዛት ኖሮት ሳይሆን የተሆንቶ ውጥንቅጥና ዘርፈብዙ ተጻረርቶዎች በያንዳንዱ ጽንስ እርግዝናና ውልደት ላይ የሚያኖሩት የቦታ፤ጊዜና ሁኔታ ማህተምና አሻራ ፍጹም ሊመሳሰል የማይችልና ልዩ በመሆኑ ነው ቢባል ከዕውነት የራቀ አይሆንም፡፡ አንድ ግለሰብ በመሰረታዊ ማንነቱ ከመላው የሰው ዘር ፤ከእናት አባቱ ልጆች እህትና ወንድሞቹ ጭምር ፍጹም ልዩ የሚያደርጉት ከላይ ከመሰረቱ ግንድ እየተገነጠለ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣበት ጉዞና ገጠምሽኞች ከመንም ሌላ ሰው ጉዞና ገጠምሽኞች ሙሉ በሙሉ እንዲገጥሙ የተሆንቶ ሕግጋቶች ስለማይፈቅዱ ፤ የገጠምሽኞቹም የማንኛውም ቁሳካል ወይንም ህይወት አድራጊ፤ገንቢ፤አብሳይና ቅርጽ አውጪ አሳዳጊና አጫጪ በመሆናቸው ውጤታቸው ሁሉ ፍጹም እራስነትን የተጎናጸፈ ማንነት ነው፡፡ ለዚህም ነው ከመላው የዓለም ሕዝብ መሀል ያንድን ግለሰብ ማንነት በዲኤንኤ አሻራው ለይተን የማውጣትን ክህሎትና በዲኤንኤ ስንክሳሩ ላይ በተጻውም መዝገብ ላይ ጉራማይሌ የዘር ግንዱን ጭምር የማንበብ ደረጃ ላይ የምንገኝው፡፡አንድ የዘር ግንዱን ለማወቅ በዚህ አዲስ ግኝት የዘር ግንድ የዲኤንኤ ጥናት የተጠመደ ጥቁር አሜሪካዊ ጥናቱ የዘሩ ግንዱ አምስቱንም ክፍላተዓለማት ማካተቱን ሲያውቅ ለካስ ቀለም የሚታየው በብርሀን ብቻ ነበር፡ ነውም ያለው ፡፡ ይህም የዘር ግንድ ስንክሳር በልዩነት ላይ ያለን አንድነትና በአንድነትም ላይ ያለን ልዩነት በሙሉቀን ብርሀን የሚጋለጥ ዕውነት ነው፡፡

ይቀጥላል

አየለ ዓለሙ ተ/ማሪያም

ጊዜያዊውና ዘመናዊው የስነ ህልው(Biology)ጥናትና ምርምር በግልጽ ማሳወቅ የቻለው መሰረስታዊ ዕውነት፤ ህልው (life)ባጠቃላይ  አዝዕርትና(plants) እንሰሳት(animals) ባጋጣሚ ከተከሰተች ከአንዲት አንድ ሴል የነበራትና ያላት የጋራ ጅምርት መነሳታችንንና በጊዜና ሁኔታዎች ልውውጦሽ አጋጣሚዎች በየርከኑ ቅርንጫፍ ሆነን በእንሰሳትነትና ተክላትነት ብሎም ተክላት በራሳቸው እንሰሳትም በበኩላቸው እየተክፋፈሉና እየተባዙ ከሁለት እነሆ ዛሬ በጉልህ አይተን ወደምንመሰክርለት ጽንፈኧእላፍነት መድረሳችንን ነው፡፡ ታዲያ ታላቁ ግርምታና አስደማሚው ትንግርት የዚህን ሁሉ ውጥንቅጥና ውስብስብ የዕድገታችን የጉዞ ታሪክ እንዳይረሳና እንዳይጠፋ በረቀቀ መልኩ ከነአዳዲስ ጭምሮቹ በማኮክድሪአል DNAችን እየተጻፈ ከጅምርቱ እስከአሁንና ወደፊትም ህልው እስካለ መቀጠሉ ጭምር ነው፡፡ እነሆ ዛሬ በዚህ ዘመናዊ የስነ ህልው የሳይንስ ጥበብ የሰው ልጅ ሁሉ ከጥቁር እስከ ነጭ፤ ከምስራቅ እስክ ምዕራብ ካንድ የጋራ ቅማንት ጅምር ተነስተን የተገነጠልንበት አንጓ የእድሜ ዘመን ጭምር አሌ በማይባሉ ማስረጃዎች የተረጋገጡበት ዘመን ላይ በመገኘታችን እውነትም የዛሬዎቹ ትውልዶች ከምንጊዜውም በላቀ መልኩ አንድነታችንንም ሆነ ልዩነታችንን ጭብጥና የማይናጋ ጠንካራ ዕውነት ላይ ለማቆም እድሉን የተጎናጸፍን ነን::ዛሬ ከቴም የአካባኢ ሁኒታዎችና ክሰተቶችን በመጣወርና በመጣመር(ENVIRONMENTAL CONDITIONING)ከፈጠራቸው ውጫዊ ገጽታዎች ባሻገር በውስጣዊ ተክለ ሰውነታችን ከቅርብ ዘመዶቻችን በበለጠ ጨርሶ ከተለምዶአዊው ባእዳን ጋር ዝምድናችን የጠነከረ ሊሆን መቻሉን በተጨባጭ ዕውነት ማየት የተቻለበትን ዘመን መኖር ጀምረነዋል፡፡

ውጫዊ ገጽታዎች እንደ ውስጣዊ ተክለማንነቶች ከቤተሰብ ተወራሽ ሆነው ሳለ ፤ ከላይ እንደጠቀስኩት ቤተሰቦችም የተቀዳጇቸው ካካባቢ ጥምረትና ጥውረት እንደመሆናቸው እኒህም ያካባቢ ሁኔታዎችና ክሰተቶች የመጀመሪያ ንክኪአችውና ተጸኖአቸው ከውጫዊ ገጽታችንና በውጫዊው ገጽታችን ላይ ስለሆነ ፤በውጫዊው ገጽታችን ላይ እንደሚታየው በውስጣዊው ተክለማንነታችን ላይ ለውጥ ከማምጣታቸው ቀድመን ተለያይተን ደግመን መገናኘት ችለናል፡፡ለዚህም አይነተኛው ምስክር ማንኛውም የሰው ዘር ከሌላ የሰው ዘር ጋር መራባትና መዋለድ መቻሉ ነው፡፡ ያንድ ግንድ (species)እንሰሳት ተለያይቶ በመኖር የጊዜ ብዛት ውስጣዊና ውጫዊ ማንነታቸው ሲጎላ ፈጽሞ መዋለድ አይችሉም ፤ ቅርበት ኖሮአቸው ቢዋለዱ እንኳን የወለዱት ዘር መቀጠል የማይችል መካን ፍሬ ይሆናል ፡፡ለምሳሌ ፈረስና አህያ ያንድ ግንድ ዝርያሞች እንደመሆናቸው መዋለድ ቢችሉም ልጆቻቸቸው ግን መዋለድ አይችሉም ፡፡ ስለሆነም የበቅሎ አባቷ አህያ እንጂ በቅሎ ሆኖ አያውቅም ፡፡ ልዩነትና አንድነታቸው እስከዚያ ድረስ ነው ፡፡ነጭ አህያና ጥቁር አኅያ ፤ነጭ ፈረስና ጥቁር ፍረስ ቢዋልዱ ትውልዱ ቀጣይ ነው፡፡ፈረስ ሁሉ ፈረስ አህያ ሁሉም አህያ በመሆኑ፡፡

የስነ ህልው እድገት ያንድ አቅጣጫ የወደፊት እድገት ነው፥በመሆኑም ህልው ቅርንጫፍ ሆኖ ከግንዱ ከተለየ ተመልሶ ከነበረበት መደባለቅ ያስገነጠለውን ብልጫ ወይንም እንሰት ሊያሳጣው ቢያንስ ሊበርዝበት ስለሚችል ለግንጣዩም ሆነ ለዋናው ግንድ የሚኖረው ፋይዳ አመርቂነት ስለሌለው ተሆንቶ የአብረን እንጥፋ ወይ አብረን ባለንበት እንሂድ ለሚመስለውን አካሄድ  ግደባ ጥላበታለች። ለምን ቢባል ተገንጥሎ መመለስን ተሆንቶ ፈቅዳ ቢሆን ተራራ ወጥቶ ተመልሶ ዘብጥ ማረፍ ያህል የሲሲፈስ ጥረት በሆነና ህልው ባንድ ሴል ጀምሮ ባንድ ሴል በቀረ ነበር። ያ ሳይሆን ቀርቶ ህልው ሁኔታዎች፤ጊዜና ዕድል በሰጡት አጋጣሚዎች ባገኘቻቸው ፋይዳዎች ቅርንጫፍ እያወጣች እነሆ ካንዲት ባለአንዲት ሴል ህልው እስከ ታላቁ የሰው ልጅ መድረስ ተችሏል።ከዚህም መረዳት የምንችለው ሌላው ሀቅ ተሆንቶ የኪሳራ ኪሳራ፤ የኪሳራ አትራፊ ጨዋታ ሳይሆን ያትራፊ አትራፊ፤አንተም በሚናህ እኔም በሚናዬ ትርፌንም ለራሴ ኪሳራዬም የኔ  የሽቅድድም መርህ እንደምትጓዝ ነው። ታዲያ ይህንን እሽቅድድም በብጤዎች መሀል ያግድም ትብብር የለም ወይንም አልነበረም ማለት እንዳልሆነ እንዲጤን ማሳሰብ አግባብነት እንዳለውም ይሰማኛላ።እንዲያውም ያግድም አግድም የብጤዎች ትብብር ለሽቅብ ቁልቁል የእርከን እድገት ውድድር አይንተኛውንና ወሳኙን ሚና ተጫዋች ትውንት ነው።

11/21/18

  ምንም እንኳን የብጤዎች የኔ እበልጥ እኔ እሽቅድምድም ሂደቱንና ግብአቱን ያለአጥኖትና ያለ በቂ ግንዛቤ አግልበው ሲያዩት የሽቅብ ቁልቁል የርከን ሽኩቻና የጥፍፊ ርኩቻ ቢመስል፤የማሸነፊያውም ሆነ የመሸነፊያው የውድድር አውድ ጠቀሜታውና ጉዳቱ ያግድም መሰል ማህበረስቡን ካላካተተ ሽንፈቱም ሆነ ስኬቱ ላሸናፊውና ባሸናፊው ላይ ተወስኖ የሚኖረው ፋይዳ ትርጉም አልባ ይሆናል::በብጤዎች መሀል ለሚደረጉ ውድድሮች ዳኚውና እውቅና ሰጪው ብጤውና ያግድም ማህበረሰቡ አባል እንደመሆኑ ያሸናፊው ልዩ ብቃትም ሆነ ክህሎት ማህበረሰቡን ቢያንስ በተወስነ የግንዛቤ ወይንም ቁሳካላዊ ስኬት ደረጃ ወደፊት እንደሚያራምደው አዎንታዊ አስተዋጻኦ እንዳለው ወይንም እንደሚኖረው በመገንዘብ ነው::ታላቁና ዋነኛው የብጤው ማህበረሰብ(SPECIES) ሁሉን አቀፍ ተሆንታዊ ትጋት (NATURAL PREOCCUPATION) የማህበረሰቡ ለትውልድ እንደትውልድ መቀጠል ስለሆነ የውድድሩ ሁሉ መደምደሚያና ያሸናፊነቱ መለኪያ በግልጽና በውስጠ ታዋቂነት ለዚሁ የትውልድ ተቀጥሎሽ ይነስም ይብዛ የሚኖረው አዎንታዊ አስተዋጾ መሆኑን በአጽኖት መገንዘብ አንዳንድ ሰዎች ዳርዊናዊውን የሽቅድድሞሽ ጨዋታ የውሻው ውሻውን በላው የመበላላትና የጥፍፊ ብቻ አውድ አድርጎ እንደሚሰብክ ከሚያስመስሉት የቁንጽል ክህሎት ስህተት ይታገደናል::

   የሰው ልጅ ከሌሎች የቅድመ ትውልድ ብጤውቹ ተለይቶ እያደነ፤እያለማና እየረባ ብሎም እነሆ ዛሬ እስከደረሰበት የረቀቀ የሳይንስና ተክኖሎጂ ክህሎትና ትጠቃሚነት ደረጃ የደረሰው በብጤዎቹ ያግድም አግድም የቡድንና የግለሰብ ውድድርና ሽንንፍ ሽንፈትን መቀበልና አሸናፊንም እውቅና ሰጥቶ ሾሞ ሸልሞ የግኝቱና ክህሎቱም የጋራ ተጠቃሚ በመሆን እንጂ ግኝትችና ክህሎቶች ሁሉ ባንድ ጊዜና በሁሉም ተከስተው አይደለም :: ምንም እንኳን ግኝቶችና ልዩ ክህሎቶች  ሁሉ ባብዛኛው ጅምራቸው ያቸናፊ ግለሰቦች ቢሆኑም ላብዛኝው ተዳርሰው ባብዛኛውም ተቀባይነት አግኝተው ህብረተሰቡ እንደህብረተሰብ ለትውልድ መቀጠሉ ለሚያደርገው ጥረት አሉታዊ አስተዋጽኦ ስለሚያበረክቱ በጊዜ የጋራ እውቀቶች፤ የጋራ ክህሎቶችና እሴቶች ይሆናኩ:: 

          

11/21/18

Adnesine( A) ,Thymine(T), Guanine(G)and Cytosine (C)

ATGC

     የህይወት ሁሉ የታሪክ  ስንክሳር ከመጀመሪያዋ አንድ ሴል እስከ እጅግ ውጥንቅጡና ረቂቁ የሰው ልጅ የህልውና ማንነት የተጻፈባቸውና የሚጻፍባቸው  ፊደላት ከላይ በተመለከቱት አራት መደብ ባላቸው ዲአኦክሲ ኒኩላይክ አሲድ (ዲ ኤን አኤ) በተሰኙ ኬሚካሎች ሲሆን፤ እያንዳንዱም እራሱን የቻለ ማንነት ያለው ህልው ከመጀመሪአዋ የህልውና ሁሉ መጀመሪያ ህለው እስካለንበት ዘመንና ማንነት፤ የየግል ማንነቱንና ማንነቷን ታሪክ ከቤተሰብ በጋራ የወረሱትን እንዳለ እየወሰዱ የየራሳቸውን እየጨመሩበት ለቀጣይ ትውልድ እያወረሱት የመጣ በጥቅሉ ሲታይ የግለሰቦች ትርክት ነው።

    ባ4ቱ ፊደላት የተጻፈውና የሚጻፈውም የተክለማንነት ድርሰት በተለያዩ ግለሰቦች በ24ቱ የእንግሊዝኛ ፈደላት ወይንም በታወቁቱ የግእዝ ወይንም ሌሎች ፊደሎች እንደሚጻፉ ድርሰቶች በይዘትና አገላለጽ አይነተኛና ልዩዎች ናቸው። ህልው ሁሉም ወዶና ሳይወድ የራሱን የውስጥና የውጭ ተክለማንነቶች ጸሀፊ በመሆኑ ኖሮት አውርሶ የሚያልፈው ፍጹም ከሌላ የማይመስል የራሱንና የራሱን ብቻ ስንክሳር ነው። ያንድ ሙሉ ማንነት ያለው ህልውም እያንዳንዷ በመላ አካሉ ውስጥ የምትገኝ ሴል የሚሰለች በሚመስል ድግግሞሽ የስንክሳሩን ሙሉ ግልባጭ ስይጨመርበትና ስይቀነስበት የተጻፈባቸው ቢሆኑም እንደየ ልዩ ሙያቸው ግን የመጉላትና ያለመጉላት ባህርይ ይከሰትባቸዋል::

    የሚገርመውና አንዱ ትልቅ ትንግርት የተወረሰው ሳይደለዝና ሳይሰረዝ እንዳለ እየተጠበቀ የወራሹ እየተጨመረና እየትወረሰ በመቆየቱ እነሆ ዛሬ ካለንበት ተነስተን ታሪካችንን እስከጀመርንበት መቁጠርና ዝምድናችንንም ማወቅ የቻልንበት ዘመን እውን ሆኖአል። ሁለት ግለሰቦች ባያታቸው አንድ ቢሆኑ በሁለቱም ግለሰቦች የታሪክ ስንክሳር የወላጆቻቸውን የተለያየ ትርክት ይጨመርበታል እነርሱም የራሳቸውን ቢጨምሩቡትም ያያታቸው ግን ሳይደለዝና ሳይሰረዝ በቋሚነት ይቀጥላል::ፈረንጆቹም የልጅ ልጅ ለማየት የሚኖራቸው ህልምና ፍላጎት ሲሟላላቸው ጂኖቼ ብጊዜ ወንዝ ሲፈሱ አይቻለሁ ብለው እርካታቸውን የሚገልጹት ለዚህ ይመስለኛል::

   12/03/2018

የሽሮዲንገር ግራ መጋባትና የቀውስና (chaos)ስር አት(order)ጽምረትና ልዩነት፡፡
አንዳቸው ካንዳቸው ተነጥለው መከሰት የማይሆንላቸው አንዳቸው በተናጠል ገዝፈው የሌላውን መኖር አይችሉም እንጂ ማሳጣት ቢችሉ ሁለንተና እንደምናውቀውና እንደምንኖረው ሕያውና ቅጽበታዊ ተለዋውጭ መሆኑ ቀርቶ የማይንቀሳቀስ፤ ሙትና ፍጹም የረጋ ህይወትም የሌለውና ህይወትም የማትሆንበትበሆነ ነበር፡፡ቀውስ ባለበት ሁሉ ስርአት አስፈላጊ(neccesary)ይሆናል፤ ስርአትም ሌላዙር ቀውስ አስክትሎ ይመለስና በማያቋርጥ ቅብብሎሽ አንዱ የሌላውን መከተል እያስገደደ እነሆ ከደቂቅ እና ረቂቅ እስከ ግዙፍና አጥናፍ ላለንበትና ለምንኖርበት የሁለንተና እውነት ሞተር ነው፡፡ ታዲያ ትልቁ ግራ መጋባት የሚነሳው እንዴትስ ስር አት(order)ከቀውስ (chaos)ሊከሰት መልሶስ ከስር አት ከቀውስ ይከስታል የሚለው አብይና የሁለንተናን በተለይም የሕልው አይነትኛ መገለጫ የሆነውን እንቅስቃሴ(motility)መንስኤና ምክንያት በማያወላዳ መንገድ መልስ የሰጠው የሁለተኛው የቴርሞዳይናሚክስ (የሙቀትና ቅዝቃዜ ቅጽበታዊ እንቅስቃሴ ሁለተኛው ህግ)ባግባቡ በስፋትና ጥልቀት መመርን ይሻል፡፡ ህጉም እንደሚከትውልው ይደነግጋል
ሀ)ተሆንቶአዊ አካላት ሁሉ ያላቸውን ጥቅም ሰጪ የሀይላቸውን ክምችት የመቅነስ ተሆንቷዊ ዝንባሌ አላቸው ዕድሉም ሲገጥማቸው ይጠቀሙበታል፡፡
ለ)ቁስ ከክፍተኛ የኃይል ክምችት ማማ ወደ ዝቅተኛ የኃይል ክምችት ሸለቆ ያለ ውጫዊ ተሳትፎ በራሱ ይወርዳል፡፡በሂደቱም  የነበረውን ትርፍ ጥቅም ሰጪ የሀይል ክምችት ይቀንሳል።ትርፍ ጥቅም ሰጪ የሃይል ክምችት ያለው ቁስ እንደየክምችቱ መጠን በነውጥና ቀውስ የታወከ ስለሆነም በሚያደርገው ይህንን ክምችት ብሎም ቀውስ የመቀነስ ዝንባሌ ሃይሉን ከነ ቀውሱ  ቁልቁል ሲንደረደር በመንገዱ ላይ ለሚገጥመው ቁስ እያጋባ ወርዶ ከዝቅተኛው የሃል ማማ ያርፋል።
ሐ)ቀውስ ክፍተኛ የኃይል ክምችት ማማ ሲሆን ስርአት ዝቅተኛው የኃይል ክምችት ሸለቆ ነው፡፡
መ)ሙቀትና ቀውስ የኃይል ክፍተኛ ክምችት (high entropy)ገጽታዎች ሲሆኑ ቅዝቃዜ ባንጻሩ የዝቅተኛ ኃይል ክምችት (Low entropy)ገጽታዎች ናቸው፡፡ ታዲያ በሁለንተና  ያለው የኃይል በየማይክሮ ሰኮንዷና በየናኖ ቴምፐሬቸሯ የምትከሰተው የኃይል ክምችት ልዩነቶች መንስኤ በቁስና ህልው ላይ የምታሳድረው የራሷ  የጥመት፤ የመቅናት፤ የመጠን፤ ያቅጣጫ ፤የጥንካሬና የልስላሴ አሻራ ልዩ የግል ማንነት የሚባለውን መገለጫ ተክለማንነት ያጎናጽፉታል።

ይቀጥላል

አየለ ዓለሙ ተ/ማሪያም

Cybernatian

This entry was posted in posts. Bookmark the permalink.

1 Response to ግለስበዕና

  1. Pingback: ግለስበዕና | Continuum @ Cybernatian

Comments are closed.